Equipment and Accessories

በአርሲ ዞን የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

በአርሲ ዞን የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለጽሕፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ)፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለፅዳት እቃዎች፣ እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000064687607 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ማስወገድና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

4.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ በወረዳው የስብሰባ አዳራሽ ወይም በግዥ ክፍል ይከፈታል። ነገር ግን ይህ ቀን በዓል ወይም ሰንበት ለይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽሕፈት መሣሪያዎች፤ ለደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) እንዲሁም፤ ለፅዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ)፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።

6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ኦጎልቾ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።

7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 09 11 80 38 82, 09 44 78 87 73 እና 09 00 26 29 69 & 09 72 87 12 66
በአርሲ ዞን የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-31 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Arsi Zone Zwai Dugda District Cash Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T07:25:48.000Z
← Back to all tenders