Stationery
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪየመ/ደ/ት/ቤት የ2019 በጀት ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- የፅህፈት መስሪያ እቃዎችና ሌሎች
- ሎት 2፡- የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3፡- የደንብ ልብሶች
- ሎት 4፡- የላብራቶሪ እቃዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያና እና መፅሐፍት
- ሎት 5 የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት6፡- የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት7፡- ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ ዕድሳትእና ጥገና፡ ለህንፃ ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ ዕድሳት እና ጥገና፡ ለመስረተልማት ዕድሳት እና ጥገና።
- ሎት 8፡- መስታንግዶ ከነ ሙሉ መብሳያ እቃ
- ሎት9፡ ጭነት
1.ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ እቃዎች በፎቶ እና ገዥው መ/ቤት ድርጅታችሁ በአካል መጥቶ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፊቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለበት።
5. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጀሞ2 ሸገር ማዞሪያ 200 ሜትር ገባ ብሎ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አከባቢ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የጋራፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ ስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ( ሎት1 )13,620 አስራ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ብር(ሎት2) 10,455 አስር ሺህ አራት መቶ ሀምሳ አምስት ብር (ሎት3) 10,664 አስር ሺህ ስድሰት መቶ ስልሳ አራት ብር (ሎት4) 1500 አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር (ሎት5) 50,000 ሀምሳ ሺህ ብር (ሎት6)1000 አንድ ሺህ ብር(ሎት7)16000 አስራ ስድስት ሺህ ብር (ሎት8) 2000 ብር ሁለት ሺህ (ሎት9) 1500 አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ሲሆን በተረጋገጠ ሲፒኦ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀን 2፡30 እስከ ቀኑ10፡30 በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል/
7. ተጫራቶች በሚወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ጨረታ ከመከፈቱ ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
8 ተጫራቶች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልፅ መሙላት አለባቸው።
9.ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 1% በባንክ /cpo/ በተረጋገጠ ቼክ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በዋላ ባቀረቡበት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችልም። በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዢ ፈፃሚ አካል ማስያዝ አለባቸው። ያስያዙትን ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከወጡና ውሉ ተመላሽ ሲደርጉ ነው።
11. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. እቃውን የሚያስገቡበት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6 ሰዓት ሲሆን ከ ሰዓት 7 እስከ 9 ሰዓት ድረስ መሆኑን እናሳውቃለን። በተጠቀሰው ሰዓት ዉጪ የሚመጡ ከሆነ የማናስተናግዳቸው መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሽ፡- በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቱ ልዩ ቦታው ጀሞ2 ሸገር ማዞሪያ ወደ ወስጥ ገባ ብሎ 200 ሜትር አማኑኤል ቤተከርሰታያን አጠገብ
ስልክ ቁጥር 09 21 59 19 36 / 09 10 00 74 65/ 011 380 3469
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-25 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gara Furi Elementary School
- Buyer address: ልዩ ቦታው ጀሞ 2 ሸገር ማዞሪያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ 200 ሜትር አማኑኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
- Posted at: 2026-08-13T07:35:58.000Z