Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. የጽሕፈት መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃዎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች።
2. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ፈርኒቸሮች።
3. የሠራተኛ ደንብ ልብስ።
4. የመኪና ጎማና የተላያዩ መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች።
5. የኮንስትራክሽን እቃዎች
በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሟላት ያለባቸው መስፈርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው
1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ንግድ ፍቃድ ና በሕጉ መሰረት ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ።
2. የአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስከር ወረቀት ያላቸው።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የመወዳደር ሃሳባቸው ላይ በመ/ቤታችን በወጣላቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለጽ በሰም የታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 8 ለዚህ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ናሙና መታየት የሚገባቸውን ዕቃዎች በናሙናና በፎቶግራፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት የጠበቀና በተሰጠው እስፔስፍኬሺን መሰረት ኦርጅናል ዕቃ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ጥራቱ ያልተጠበቀና ኦርጅናል ያልሆነ ዕቃ ካቀረቡ የመመለስና መቀየር ግዴታ ይኖርበታል።
9. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
10. የተጠየቁት እቃዎች ሞዴል በተጠየቀው እስፔስፊኬሺን መሰረት ተሞልቶ ካልቀረበና ማንኛውም ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የድርጅቱ ይሆናል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በተራ ቁጥር 1. 20000፣ በተራ ቁጥር 2. 20000፣ በተራ ቁጥር 3.8000፣ በተራ ቁጥር 4.10000 በተራ ቁጥር 5. 20000 በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ብር በነንሰቦ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማስያዝ አለበት።
12. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን 26/12/2018 ዓ.ም በሥራ ቀን 11:30 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው የሥራ ቀን 27/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 8 ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታዉ ሂደት በተላላፈው ውሳኔ ተገዢ ይሆናሉ።
13. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
14. አሸናፊ የሆነ ተጫራች መ/ቤቱ በሚሰጠው የአቅርቦት ትዕዛዝ መሠረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ እና በመ/ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 37 65 99፣ 09 39 60 62 74፣ 09 08 30 35 49 ና 09 17 51 40 81 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በምዕራብ አርሲ ዞን የነንሰቦ ወረዳ ፋይናንስ /ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 17:30
- Bid opening: 2026-09-02 09:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: West Arsi Zone Nensebo Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
- Posted at: 2026-08-13T07:55:05.000Z