Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገንዘብ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣ ቋሚ እቃዎችን፣ የህንፃ መሳሪያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና የደምብ ልብሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገንዘብ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፤ ቋሚ እቃዎችን፤ የህንፃ መሳሪያዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ና የደምብ ልብሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ፡-

1. በዚህ ስራ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ገንዘብ ቤት የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ተጫማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታውን ሰነድ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ገ/ቤት በጅማ ገነቲ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር.2 የማይመለስ ብር 1000(አንድ ሺህ) ከፍለው ጨረታው ከወጣበት ቀን ነሐሴ 7/12/2018 ዓ.ም ተከታታይ 15 የስራ ቀናት መካከል በየቀኑ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 500,000/አምስት መቶ ሺህ /ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።

6. የሚያቀርቡትን የዋጋ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን 7/12/ 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 28/12/18 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው ነሐሴ 28/12/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 በጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በራሳቸው ወጪ እቃውን የሚያቀርቡት በጅማ ገነቲ ወረዳ ሐረቶ ከተማ ገ/ኢ/ል/ት/ቤት ድረስ ይሆናል።

10. በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው የእቃው ብዛት (Quantity) 20% ለመቀነስም ሆነ ለመጨመር መስሪያ ቤቱ ሙሉ መብት አለው።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-10 42 09 29, 09-20 41 51 63, 09 11 59 93 93

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-03 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Horo Guduru Wollega Zone Jimma Geneti Woreda FEDB
  • Bid bond: 500,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T08:05:27.000Z
← Back to all tenders