Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የተለያዩ የጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድረን መግዛት ይፈልጋል

Description

የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና የተለያዩ የጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድረን መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያላቸው ሆነው፤

ሀ. የዘመኑን ግብር በመክፈል የታደሰ ንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ

ለ ከገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢነት የሚዝገባ የምስክር ወረቀት መረጃ የሚያቀርብ

ሐ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

2. በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ በአንድ ሰነድ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 10,000 ብር (አስር ሺ ብር) በደራ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. የጨረታዉ የመወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና አንድ የኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር ተያይዘዉ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይቀርባል።

4. ተጫራቾች የሰጠናችሁ ሁሉንም ሰነድ ሙሉ አድራሻ የተገለጸበት ሆኖ በሚመለከተው ባለስልጣን (ህጋዊ ዉክልና ባለዉ አካል) የተፈረመበትና በማህተም ተረጋገጦ መቅረብ አለበት።

5. የጨረታውን ሰነድ በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 የስራ ቀናት በአንድ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ የያዘ ፖስታ እስከ 16ኛው ቀን በማቅረብ ጨረታውን የያዘው ሳጥን በዚያው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል። ምናልባት 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተዘግቶ ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት አያግድም።

7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

8. የጨረታው ውድድር በአይነት መሆኑን ይታወቅ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 115 0061/199 ፣ 09 12 79 58 41 መጠየቅ ይቻላል።

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-31 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Dera Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በአንድ ሰነድ
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/ በአንድ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T08:18:07.000Z
← Back to all tenders