Equipment and Accessories
በምዕራብ ወለጋ ዞን የመነሲቡ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓ/ም ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉትን የጽ/መሳሪያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲውም የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የመነሲቡ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓ/ም ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉትን
- የጽ/መሳሪያዎችን
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲውም የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
1. የ2018 ግብር የከፈለና 2019 ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ
2. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
3. ቲን ተመዝጋቢ የሆነ
4. የ2018 ግብር መክፈሉን የሚገልጽ ክሊራንስ ወይም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
5. ከመንግስት ግዥ በቅጣት ያልተከለከለ
6. ጨረታ በአየር ላይ የሚቆይበት 15 ስራ ቀን ሲሆን ከ7/12/2018 እስከ ከ27/12/2018 የሚቆይ ሲሆን በዚያው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግ በዚው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል።
7. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተወዳደሪዎች አለመገኘት ጨረታውን እንዳይከፈት አያግድም፤
8. የጨረታው ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በአንድ ፖስታ ሆነው የፋይናሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ የሚቀረቡ ሲሆን የቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ ግን አይታሽግም።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዋጋ ካገኘው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ምዝገባው የሚካሄድበት ቦታ መነስቡ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሆኖ የግዥ ስራ ሂደት ክፍል ይሆናል።
11. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር ብቻ ሲሆን የጨረታ ማስያዣ ወይም cpo መንዲ ከተማ ባሉት ቅርንጫፍ ባንኮች ማስያዝ ይችላሉ።
12. የጨረታ ተወዳዳሪዎች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከመነስቡ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሰነድ ማግዛት አለበት።
13. ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈ ተወዳዳሪ እስከ መነሲቡ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ዕቃዎችን ማምጣት ግዴታ አለበት።
14. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ዕቃውን ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
15. ጨረታ የሚከፈትበት ቦታ መነሲቡ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይሆናል።
ተጨማሪ መረጃ ለመግኘት ስልክ ቁጥር 09 17 17 51 99 ወይም 09 13 47 88 39 መደወል ይችላሉ።
በምዕራብ ወለጋ ዞን የመነሲቡ ወረዳ ገ/ ጽ/ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-02 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: West Wollega Zone Menesibu Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
- Posted at: 2026-08-13T08:22:25.000Z