Stationery

በኢሉባቦር ዞን የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ 

በኢሉባቦር ዞን፣ የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት፣ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዘመን በወረዳ ስር፣ ለሚገኙ መስሪያበቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • 1. የፅሕፈት መሳርያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎች
  • 2. ኤሌክትሮኒክስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች)
  • 3. የደንብ ልብሶችና የስፌት ዋጋ
  • 4. የመኪና ጎማና የሞተር ሳይክል ጎማ
  • 5. የማሽን ክራይ ማለትም ዶዘር፣ግሬደር፣ ሩሎ፣ ዳምትራክ ፣ ስካቫተር

በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መሰፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. በዘርፉ ንግድ፣ ፍቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የቲን ነምበር ያላቸውና የ2018 ዓ.ም የመንግስት ግብር ከፍለው ያጠናቀቁና ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3. የሚቀረበው ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ኦርጅንልና ኮፒ) ሆኖ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ (በዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አከውንት ቁጥር 1000056003987 ገቢ አርገው የባንክ ስሊፕ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ወይም የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስተው ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ በኢሉባቦር ዞን ከዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ክፍል የአንዱ ሠነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ።

7. ጨረታው የሚከፈተው ለፅሕፈት መሳርያዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎች በ28/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን ለኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸሮች) በ28/12/2018 ዓ.ም ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሆኖ ተወካዮች ህጋዊ የውክልና ደብዳቤና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው። ለደንብ ልብሶች፣ ለደንብ ልብስ ስፌት ዋጋ ለተክኒክና ሙያ ሥልጠና የሚያገለግሉ መሣሪያዎች፣ የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ በ29/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

8. የዕቃ ማሰረከቢያ ቦታ የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ መገጣጠምያ፣ ማስጫኛና ማውረጃ ትራንስፖርት ወጪ በአጠቃላይ የሻጭ ግዴታ ናቸው።

9. ክፍያ የሚደረገው የተጠየቁ ዕቃዎች በጠቃላይ ገቢ ሲሆኑና እንደ ኤሌክትሮኒክስ ያሉ ዕቃዎች በባለሙያ ታይተው ተቀባይነት ሲያገኙ ብቻ ክፍያው ይደረጋል።

10. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

11. የዕቃ ብዛት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

12. የተጠየቀው ዕቃ በተጠየቀው ሰነድ መሠረት ሞልተው ማቅረብ እና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ አለበት ፤ ያልተጠየቀውን ዕቃ ቢሮ ካዘጋጀ ሰነድ ውጭ/በሌላ/ ካቀረበ እንድሁም ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

13. አሸናፊ ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ከፋክቱር ጋር አዘጋጅተው ማቅረብ የሚችሉ (ዕቃዎቹና ፋክቱር) መለያየት የለበትም።

14. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃዎች በተለይ የደንብ ልብስ እንዲመረጥ ዘንድ ማለትም ለናሙና የተለያዩ ከሦስት ዓይነት ያላነሰ ጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም ጫማ ከሦስት ያላነሱ ማቅረብ አለባቸው።

15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ማሳሰብያ፦ የማሽን ኪራይን በተመለከተ ወረዳችን ዝናባማ ስለሆነ ጨረታውንለሚትወዳደሩ ተጫራቾች ሰነዱን፡ ገዝታችሁ ብሮው በጠራችው ሰአት ቀርባችሁ የሚትወዳደሩ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ 09-13-37-75-82/ 09-17-83-09-27

በኢሉባቦር ዞን፣ የዲዱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት፣


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-09-04 14:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Illubabor Zone Didu Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የአንዱ ሠነድ ዋጋ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T08:28:20.000Z
← Back to all tenders