Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለሁሉም የሥራ ሂደቶች የሚውል የቢሮ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ አላቂ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የቢሮ የፅዳት ዕቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ አላቂ ዕቃዎች ግዥ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለሁሉም የሥራ ሂደቶች የሚውል የቢሮ የፅዳት እቃዎች የኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ አላቂ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት -1 የቢሮ የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት -2 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ፣
  • ሎት -3 የቢሮ አላቂ እቃዎች ግዥ

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ ፦

1. ለሥራው ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፤ ለሥራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ግዥው ከ200,000 ሺብር በላይ የሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለበት ።

2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 15 (ለአስራ አምስት / ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘውትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው /16 ቀን/ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የቢሮ የፅዳት እቃዎች የኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ አላቂ እቃዎች ግዥ ጨረታ ሰነድ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው 22/12 /2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የቢሮ የፅዳት እቃዎች የኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ አላቂ እቃዎች ግዥ ላይ በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ሎት 1 - 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ሎት 2፡ 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት 3፡ 10,000/አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።

6. ለቢሮ የቢሮ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ አላቂ እቃዎች ግዥ የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።

7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-28 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kemise City Administration Urban and Infrastructure Development Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T08:48:53.000Z
← Back to all tenders