House and Building Sale

ድጋሚ የወጣ የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ ነጻነት አቡ እና የፍ/ባለዕዳ አሽብር ሰይድ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 119950 በ10/04/2018ዓ/ም በመ/ቁጥር/124331 በ19/5/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት ቤት በአቃቂ ቃለቲ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤ/ቁ/354 በወራሾች ስም በእነ አሸብር ሰይድ በሚል በሴሪ ቁጥር 108111 እና በካርታ ቁጥር 011693/1 የቤቱ ስፋት 30 ካ/ሜ እንዲሁም በጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው የቦታ ስፋት 63.75ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,047,001.25 (ሁለት ሚሊዮን አርባ ሰባት ሺህ አንድ ብር ከ25/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 124331 በቀን 02/11/2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 511,750.31 (አምስት መቶ አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ከ31/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፤ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውነት ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾችከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶችውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-18 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T08:57:29.000Z
← Back to all tenders