Stationery
በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 በጀት ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 በጀት ዘመን ለወረዳው ለተለያዩ መሥሪያቤቶች የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፤ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፤ የግንባታ ዕቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክሶች፤የጽዳት መሣሪያዎች፤ ህትመትና የህትመት መሣሪያዎች፤ የመኪና ጎማና ከነመዳሪ፤ ሞተር ሳይክል ጎማና ከነመዳሪና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ።
1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው
2. የዘመኑ የ2019 ግብር የከፈለና ፈቃዱን ያሳደሱ
3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
4. 7.5 ቫት እንሰበስባለን
5. አሸናፊዎች ለሚያቀርቡት ዕቃ TOT (3%) የመክፈል ግዴታ አለባቸው።
6. በአቅራቢዎች መዝገብ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
7. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው።
8. ጨረታው የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በባቦ ገምቤል ገቢዎች ባለስልጣን ከፍለው ሰነዱን ከባቦ ገምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ የሚችሉ።
9.ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
10. የጨረታው አሸናፊ ዕቃውን እስከ ባቦ ገምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የዕቃ ግምጃ ቤት በጊዜው ማቅረብ የሚችል።
11. ተጫራቾች የጨረታው የፋይናንስና የቴክኒክ ሰነድ ያለምንም ስርዝና ድልዝ ከሞላ በኋላ በተለያየ ፖስታ አሽጎ በኮፒና በኦሪጅናል ማቅረብ አለበት።
12. አሸናፊው ዕቃውን በጥራት ማቅረብ መስጠት አለበት።
13. ካስፈለገ ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለበት።
14. የማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ የሚረዳቸውን አስፈላጊ ዶክመንቶች ካላቸው ማስገባት አለባቸው።
15. የጨረታው ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 የሥራ ቀናት ከባቦ ጋምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማግኘት የምትችሉና በዚያው ቀን የጨረታው ማስገቢያ ሣጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎችና ሕጋዊ ውክልና ባላቸው ፊት በይፋ ይከፈታል፤ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
16. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-057-117-0005 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 የሥራ ቀናት በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-05 10:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 የሥራ ቀናት በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: West Wollega Zone Babo Gembel Woreda Finance Office
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
- Posted at: 2026-08-13T09:01:09.000Z