Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚውሉ፤ ሎት 1. የጽኅፈትና የጽዳት መሣሪያዎችን፤ ሎት2 የደንብ ልብስ መሣሪያዎች፤ ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፤ ሎት4, የግንባታ ዕቃና ሎት 5. የመኪና ጎማ መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ፤
1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ2018 ግብር የከፈሉ።
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር መረቀት ያላቸው።
4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
5. ጽ/ቤታቸን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች እንዳስፈላግነቱ በቀረበው አንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ብዛቱን ማዘዝ ይችላል
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው መግዛት ይቻላል።
7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በፖስታ ከታሸጉ በኋላ ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዝብ ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል።
8. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማቅረብ በባለሙያ ታይቶ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል።
9. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጠር ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
10. የዕቃዎቹ ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹ ግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ ቦኋላ ነው።
11. ጨረታው ነሐሴ 7/12/18 - ነሐሴ 28/12/18 ቆይቶ ጨረታው ሣጥን ይዘጋል፡ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዝብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 የሚከፈት ሲሆን፣ተጫራቾች ቢገኙም በይገኙም ጨረታውን አስያስተጓጉልም።
12. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሎት1/20,000ብር፤ ሎት 2/20,000 ብር፤ ሎት 3/25,0000 ብር፤ ሎት 4/ 20,000 ብር፤ 5/ ሎት 5፣ የመኪና ጎማ 25,000 ተመላሽ የሚሆን ብር የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
14. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ ኖርበታል።
15. ማነኛውም ተጫራች ለሚያቀርበው መሣሪያ ብራንድና ማርኩን ግልጽ አደርጎ በሠነድ አያይዞ ማቅረብ አለበት።
16. እንደ አስፈላጊነቱ ከተጫራቾቹ አሸናፊ የሆኑ ጋር የውል ስምምነት እስከ መጋቢት 30/2019 ሊቆይ ይችላል።
17. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች ለውጪ ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
18. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች የጨረታውን ግዴታ ባይመጣ ለውል ማስከበሪያ 10 ያስያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤት ገቢ ይሆናል።
19. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች ለደንብ ልብስ ጨረታ የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ናሙና/ Sample/የማቅረብ ግዴታ አለበት፤ በተጨማሪም የሚቀርበው ናሙና የተጠየቀ ብቻ መሆነ አለበት
20. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ
ስልክ ቁጥር 09 17 09 37 49 / 09 22 42 96 65, 09 17 29 95 70
የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ነሐሴ 28/12/18
- Bid opening: 2026-09-03 10:30
- Bid opening (note): ነሐሴ 28/12/18 በ4፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Nejo City Administration Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
- Posted at: 2026-08-13T09:04:24.000Z