Stationery

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/12/2019

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • 1. ሎት 1 እስቴሽነሪ
  • 2. ሎት 2 የመኪናና የሞተር ጎማዎች
  • 3. ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
  • 4. ሎት 4 የደንብ ልብሶች
  • 5. ሎት 5 የጽዳት እቃዎች
  • 6. ሎት 6 ሞተር ሳይክል

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች:-

1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፈቃድ ያሳደሳችሁ እና ታከስ ክሊራንስ ማቅረብ የምትችሉ።

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ።

3. በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሎት2 ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 4 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 5 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ለሎት 6 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንት በእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።

5. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው

6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾቸ ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።

8. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታው ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከ7/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/12/2018 እስከ 8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

10. ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉለውም፣

11. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60/ስልሳ/ ቀናት ብቻ ይሆናል።

12. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይዛወራል።

13. 7.5 ቫት ዊዝ ሆልድ የምንቆርጥ መሆኑን።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር በ09 10 10 67 16 ወይም 09 28 01 17 46 ይደውሉ።
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ጉንችሬ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-27 14:10
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Enor Woreda Finance Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T09:07:20.000Z
← Back to all tenders