Stationery

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ወለጋ ዞን የጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፤ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፤ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ አላቂ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችና መቀመጫዎች እና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ዕቃዎች፤ ሞተር ሳይክሎችና የተሽከርካሪ ጎማዎች ለወረዳው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ወለጋ ዞን የጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት ፡ በወረዳዉ ለሚገኙ መ/ቤቶች

  • የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች ፤
  • የሠራተኞች ደንብ ልብስ ፤
  • የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፤
  • አላቂ እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችና መቀመጫዎች እና
  •  የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ዕቃዎች ፤
  • ሞተር ሳይክሎችና የተሽከርካሪ ጎማዎች ለወረዳው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-

  1. የ 2018 ወይም 2019 ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው ::
  2. ቲን ነምበር (TIN ) ያላቸው፣ ቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  3. የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለዉ።
  4. የአቅራብነት የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፡፡
  5. ማንኛዉም ተጫራች የ2018 ግብር መክፈሉን የሚገልፅ ከገቢዎች ባለስልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  6. ጥራት ያለዉን ዕቃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸዉ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር የሚገልጽ ዶክሜንት (Specification of Materials ) የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር ) ለጉደያ ቢላ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ከፍለው የጨረታውን ሰነድ በጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ክፍል ቀርበው በመውስድ ዋና ኮፒ እና CPO, በተለያየ ኤንቬሎፕ በሰም የታሸገ 8/12/2018 እስከ 26/12/2018 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ::
  9. ማንኛውም ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ሥም፤ አደራሻ፣ ማሕተም እና ፊርማ ማድረግ አለባችሁ፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራቾች ከጨረታ በኋላ የሚመለስ ጨረታውን ያቀረቡትን ዋጋ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፡፡
  11. ጨረታው በ26/12/2018 ዓ.ም እስከ 2፡30 ሰዓት ቆይቶ በዚያዉም ቀን በ3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12.  መሥሪያ ቤቱ በዕቃ ብዛት ላይ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ ማዘዝ ይችላል፡፡
  13. ጨረታዉን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ካሸነፈዉ ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% ለጨረታው ስምምነት ማስከበሪያ ለግዥዉ ፈፃሚ ባለቤት ማስያዝ አለበት፡፡
  14.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ስልክ ቁጥር፡-09-11-55-40-97/09-13-83-08-88/09-13-16-37-79

የጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 08:30
  • Bid opening: 2026-09-01 09:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: East Wellega Zone Gudeya Bila Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T07:13:13.000Z
← Back to all tenders