Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው የሚያስፈልገውን የተለያዩ ግብዓት በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው የሚያስፈልገውን የተለያዩ ግብዓት በሎት አከፋፍለው
- ሎት 1 - ደንብ ልብስ ግዥ፣
- ሎት 2፡- የጽሕፈት መሣሪያ ግዥ፣
- ሎት 3፡- የሕትመት ሥራዎች፤
- ሎት 4፡- የፅዳት ዕቃዎች ግዥ፤
- ሎት 5፡- ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፤
- ሎት 6፡- የግብርና ምርት ማሳደጊያና ዘር ግዥ
- ሎት 7፡- የተለያዩ ንቅናቄ የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት 8፡- የተሸከርካር ወንበር ልብስ፤ የጎማና ሌሎች ግዥን በጨረታ ቁጥር፡- 01/2019 የ2019 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙት የተለያዩ ጽ/ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ሥራ ላይ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉት ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
የጨረታዉ መስፈርት -
1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
2. የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈለና ክሊራንስ ያለው እና የዘመኑን ንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ፤
3. VAT ተመዝጋቢ የሆነ እና ሕጋዊ ደረሰኝ ያለው
4. በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
5. በሥራ ክህሎት የተደራጁት ኢንተርፕራይዝ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን፤ ይህም የሚደረገው ከአደራጃቸው ጽ/ቤት ኃላፊ በተፈረመ የድጋፍ ዳብዳቤ ይሆናል፡፡ ከሥራ ዘርፉ እና ከሀገር ውስጥ ምርቶች ውጪ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
6. የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቆርቆሮ ፋብሪካ አካባቢ ወረዳ 2 አስተዳደር ሕንጻ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመገኘት ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ ከሰአት 11፡30 በብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በካሽ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ
- ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ፡- 62100
- ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ፡- 20,000
- ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ፡- 7000
- ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ፡- 60,000
- ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ፡- 26000
- ሎት 6 -የጨረታ ማስከበሪያ፡- 5000
- ሎት 7 የጨረታ ማስከበሪያ፡ 21000
- ሎት 8 የጨረታ ማስከበሪያ፡ 3000
በኢትዮጵያ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል የጨረታው ማስከበሪያ በየሎት በተጠየቀው መሰረት በሲፒኦ (CPO) ዋስትና በወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በሚል በማሠራት በዋናው ሰነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ በቅድመ ምርመራ ውድቅ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ በግልጽ የሚታይ እና የሚነበብ የዕቃውን ዓይነት ስም፣ የተመረተበት ሀገር፣ የሞዴሉን ቁጥር ፤ የተመረተበትን ጊዜ ያካተተ መሆን ይገባዋል፡፡
10.ግዥ ፈጻሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት እቃ ወይም አገልግሎት ላይ እንዳስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይቻላል፡፡
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት/ ንብረት ክፍል/ድረስ የመጓጓዣ አካተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12. የጨረታው ሰነድ በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሆኖ ዋና እና ፎቶ ኮፒ የጨረታው ሰነድ መቅረብ አለባቸው እነዚህም ሰነዶች በጨረታው ሲቀርቡ ድርጅቶቹ ወይም ሕጋዊ ውክልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው፤ በሰነዶቹ እና ፖስታዎቹ ላይ የድርጅቱ አቅራቢው ማህተም መኖር ይገባል፤ ሰነዱ በሚሞላበት ወቅት ስርዝ ድልዝ (ለማንበብ አስቸጋሪ) ከሆነ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
13. ጨረታውን ለመገምገም በሥራ ላይ የሚውሉትን ዘዴዎች ለዚሁ ግምገማ የሚያገለግሉትን መስፈርቶች እና እያንዳንዱ መስፈርት የሚኖረውን ድርሻ እንዲሁም ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማ እኩል በሆነ ጊዜ አሸናፊን ለመለየት በግዥመመረያው መሰረት የሚለይ ይሆናል፡፡
14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል የተከለከለ ነው፡፡
15. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆን፤ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ እንደሚወረስ እና ለወደፊቱም በመንግሥት ግዥ ጨረታ እንደማይሳተፉ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንደሚደረግ ማወቅ ይኖርበታል፤
16. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ግዥውን 10% በብር/ሕጋዊ CPO/ በወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት /woreda ዐ2 administration office/በሚል በማሠራት ማስያዝ የሚችል።
17. ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቹ /ሕጋዊ ወኪል/ በተገኘበት ተዘግቶ በ4፡30 በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወ 02 ህዳሴ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ ሕጋዊ ወኪሉ/ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽዕኖ አያመጣም። ሆኖም ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
18. ውድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውድድሩን ማሸነፉ ከታወቀ ቀን እና የቅሬታ እና አቤቱታ 7 ቀን ከአለቀ በኋላ በ15 (አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በአካል ቀርቦ የውል ስምምነት መፈረም አለበት።
19. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካለቸው የጨረታ ሰነዱ የመክፈቻ ቀን ከሶስት የሥራ ቀናት በፊት በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ።
20 ተጫራቾች በጨረታው አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው ለጽ/ቤት ኃላፊ በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
21. ክፍያን በተመለከተ አቅራቢው ዕቃውን ሙሉ በሙሉ በጥራት እና በናሙና መሰረት ማቅረቡ በቴክኒክ ኮሚቴ ተረጋግጦ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን የሚከፈል ይሆናል፤
22. ለደንብ ልብስ፣ ለጽሕፈት መሣሪያ የሕትመት ሥራዎች ለፅዳት እቃ፤ ለሌሎች አላቂ እቃ እና ለተሸካሪካሪ ጎማ፤ የወንበር ልብስና ሌሎች ተወዳዳሪዎች ምንም አይነት ምልክት ያልተደረገበት ለእያንዳንዱ እቃ አንድ ናሙና ብቻ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠየቀው ናሙና በላይ ያሉ ተጫራች በናሙና አሻሚነት ከውድድር ውጭ ይደረጋል የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ናሙናው የሚመለስም ሲሆን የአሸናፊዎቹ ተጫራቾች ናሙና ግን ያሸነፉት እቃ ሙሉ ለሙሉ አስገብተው ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ የሚመለስም ይሆናል፡፡
23. መደበኛ የጨረታው ሰነዱ በራሱ አንድ የጨረታ መመሪያና ውል መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይገባቸዋል፤
24. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
25. አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ሳይደርሱ ወረዳ 2 አስተዳደር ሕንፃ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ይገኛል፤
26. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0114622360 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki Kality Sub City Woreda 2 Administration Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
- Posted at: 2026-08-14T07:40:47.000Z