Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች የሚውል የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና ሌሎች የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች የሚውል
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ
- የጽህፈት መሳሪያዎችና ሌሎች የቢሮ እቃዎች
- የጽዳት እቃዎች
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ፈርኒቸሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ጨረታው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል፡፡
1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለ 2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ስለመሳተፍ የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
3. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ ስራ ዘርፍ ትክክለኛ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ የሚውል ብር 2000 (ሀያ ሺህ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት፡፡
5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከነሐሴ 8/12/2018 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 29/12/2018 ከ2፡30 እስከ 11፡30 የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እና አንድ ቴክኒክ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጳጉሜ 2/13/2018 እስከ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 3 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው ጳጉሜ 2/13/2018 በ4፡00 ተሽጎ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ጽፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
9 . አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ እስከ ኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሃሳቤን ቀይሪያለሁ ማለት አይቻልም፡፡
11. አሸናፊ ድርጅቶች ከሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት በማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ጨረታ የሚከፈተው የበዓል ቀን ላይ ከዋለ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር 09 13311830 /0916012874 ኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-07 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Kofele Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ የሚውል ብር 2000 (ሀያ ሺህ)
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
- Posted at: 2026-08-14T07:48:20.000Z