Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ በከተማው ስር ላሉ መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ በከተማው ስር ላሉ መ/ቤቶች አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን፤ የፅዳት ዕቃዎችን፤ የተለያዩ ህትመቶች ፤ የሞቶር ሰይከል ግዥ፤ የደንብ ልብሶች እና የስፈት ዋጋ፤ የግንባታ ዕቃዎችን፤ የከባድ እና ቀላል መኪና (ማሽነሪ) መለዋዎጫ እቃዎች የከባድ እና ቀላል መኪና (ማሽነሪ) ጎማና ባትርዎች፤ የከባድ እና ቀላል መኪና ጥገናዎች፤ የቢሮ እቃዎች የኤሌትሮኒክስ ጥገናዎች፣ የትምህርት መርጃ የስልጠና ዕቃዎች የተለያዩ የከተማ ማስዋብያ ችግኞች፣ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን ይፈልጋል፡

ስለዚህ በዘርፉ ፍቃድ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡

1. ቲን ነምበር /Tin No /እና VAT ተመዝጋቢ መሆናችሁን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡

2, ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁበትን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡

3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር /በመግዛት ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የዕቃውን /Brand Name/ መሙላት አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚው ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8.ተጫራቾች ለጽህፈት፣ ለኤሌክትሮኒክስ፣ ለጽዳትና፤ ለቋሚና ኣላቂ ዕቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100000 (መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9.ጥገና፤ ህትመቶች፤ የተለያዩ የከተማ ማስዋብያችግኞች፣ የምግብ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሀምሳ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡

10, ዕቃዎቹን ዋጋ መ/ቤቱ የሚከፍለው ንብረቱ ሙሉ በሙሉ ንብረት ክፍል ገቢ ሆኖ በጥያቄ መሠረት መቅረቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡

11, ዕቃዎቹ ገቢ ሆነው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ለአላቂ ዕቃዎች የ6ወር ለቋሚ ዕቃዎች የ1 ዓመት ጊዜ ጋራንት ዋስትና/ መስጠት የሚችልና ዕቃዎቹ የተበላሹና ኦርጅናል ካልሆኑ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ናሙና ማቅረብ የሚችል ሲሆን ሠነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም

12. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች የማጓጓዢያ፡ ማስጫኛና ማውረጃ ወጪን በመቻል ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡

13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነወ፡፡

14, ለበለጠ መረጃ ሮቤ መረጃ ሮቤ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0934 866 474 / 0912 365 294 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ሮቤ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T07:58:39.000Z
← Back to all tenders