Building Construction

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስር የሚገኘው ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስር የሚገኘው ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት

  • ሎት 1 የተማሪዎች ሪከርድ ክፍልና የማእከል እድሳት
  • ሎት 2. የቅድመ አንደኛ አስተባባሪ ቢሮ እድሳት
  • ሎት 3. የኬጂ እና የአንደኛ ደረጃ የተማሪዎች መጸዳጃ ቤት ጥገና
  • ሎት 4. የቴራዞ ንጣፍ, የልዩ ፍላጎት መሸጋገሪያ ራምፕ
  • ሎት 5. ላተራል፤ ሼልፍ፡የጠረጴዛ መሳቢያ፣ የበር መስኮትና የተማሪዎች ዴስክ ጥገና
  • ሎት 6. መጸዳጃ ቤት ማስመጠጥ
  • ሎት 7. ከለር ፕሪንተር ጥገናና ኮምፒዩተር ከፕሪንተር ጋር በኔትወርክ ማገናኘት፣ አንቲ ቫይረስ ኮምፒውተር ላይ መጫን፣ የኮፒ ማሽን ጥገናና ማባዣ ማሽን ጥገና
  • ሎት 8. ከአንድ ማእከል የሬዲዮ ስርጭት ዝርጋታ፣ የተማሪ ክፍሎች መብራት ጥገናና ሬክላም ከነላይት ቦክሱ
  • ሎት 9. ላተራል፤ ሼልፍ፡የጠረጴዛ መሳቢያ የበር፣ መስኮትና የተማሪዎች ዴስክ ጥገና
  • ሎት 1ዐ. የመማሪያ ክፍል ቀለም እድሳት
  • ሎት 11. የመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች መዝናኛ ክበብ አገልግሎት

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።

2. ለመምህራንና ለአስተዳደር ሠራተኞች ክበብ ወንበሮች፤ ጠረጴዛዎች፤ የሻይ ማሽን፤ እስቶቭ፤ የምግብ ሳህንና ትሪ፤ የእጅ ማስታጠቢያ እንስራ የመሳሰሉትን ት/ቤቱ ያቀርባል በተጨማሪም የውሃና የመብራት አገልግሎትንና የቤት ኪራይ ት/ቤቱ ይሸፍናል።

3. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ካራ ቆሬ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስር የሚገኘው የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው ሰነዱን ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመቅረብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ጥቃቅንና አነስተኛ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች የምታመጡት ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ ብቻ የተፈረመ መሆን አለበት።

6. ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7. አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን አለበት።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ

  • ለሎት 1.ብር 3000፤
  • ለሎት 2 ብር 3000፤
  • ለሎት 3 ብር 2000፤
  • ለሎት 4 ብር 2000፤
  • ለሎት 5 ብር 2000፤
  • ለሎት 6 ብር 2000፤
  • ሎት 7 ብር 3000፤
  • ሎት 8 ብር 2000፤
  • ሎት 9 ብር 2000፤
  • ሎት 10 ብር 2000፤
  • ሎት 11 ብር 2000 የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ cpo ቼክ በት/ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባችኋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ሥራ ሲጨርሱ ሥራውን ለሚያዩ ክፍሎች ማስረከብ ይኖርባችዋል።

አድራሻ፡- በኮልፌ ቀ/ክ/ከ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ልዩ ቦታው ካራ ቆሬ ከቢቂላ መናፈሻ ጀርባ / ከኮንዶሚኒየም አጠገብ

ስልክ፡- 011 369 4712 / 09 12 12 03 94

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T07:59:01.000Z
← Back to all tenders