Pesticides, Insecticides and Herbicides

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ እና በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/የአገልግሎት ግዥ

ሎት 1 ፀረ-ተባይ ማጥፊያ እና መከላከያ አገልግሎት ግዥ

ሎት 2 የታረደ የፈረንጅ ዶሮ አቅርቦት ግዥ

ሎት 3 የዓሣ አቅርቦት ግዥ

ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/ አገልግሎት ግዥ

ሎት 4 የሥጋ አቅርቦት ግዥ

ሎት 5 የገላ ሳሙና አቅርቦት ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ እቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ሰለ እቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡

7. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡

8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ይከፈታል፡፡

10. ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡

11. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሰነድ ግምገማ፣ ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 530 767 / 0115 157 337

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-26 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Filwuha Service Enterprise
  • Bid bond: 25,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:02:13.000Z
← Back to all tenders