Others

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የትራክተር ኪራይ፣ የመኪና ጎማ፣ የሕትመት ሥራዎች፣ የፀረ-ተባይ ኬሚካል፣ ፈርኒቸር (የቤትና የቢሮ እቃዎች)፣ የጽሕፈት መሣሪያ (ስቴሽነሪ) እና የተለያዩ የግብርና ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም በሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የትራክተር ኪራይ፣ የመኪና ጎማ፣ የሕትመት ሥራዎች፣ የፀረ-ተባይ ኬሚካል፣ ፈርኒቸር (የቤትና የቢሮ እቃዎች)፣ የጽሕፈት መሣሪያ (ስቴሽነሪ) እና የተለያዩ የግብርና ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም በሀገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

1. ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅደሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች

ማለትም፡-

1.1 በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ንግድ ፈቃድ

1.2 የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው

1.3 ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው

1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

1.5 ሲ.ፒ.ኦ

1.6 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ እና

1.7 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ሠአት በአፋር ብሔራዊ ክ/መ/ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት ክፍል ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

3.ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የሕጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡

4.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና /Bid Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲ.ፒ.ኦ (C.PO) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፈ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡

5.ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም፡፡

6.ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰአት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ 4፡30 ሰአት በአፋር ብሄራዊ ክ/መ/ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

7.ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8.ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር 033-366-60-22 ወይም 033-366- 33-76 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የሥራ ቀን 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-28 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የሥራ ቀን 4:30 ሰዓት
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Afar National Regional State Livestock, Agriculture and Natural Resource Development Bureau
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T07:49:40.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders