Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 13 አስተዳደር የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጨ001/19
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 13 አስተዳደር
1. ቋሚ እቃዎች 2. የቢሮ አላቂ እቃዎች 3. የጽዳት እቃዎች 4. የደንብ ልብስ 5. የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እና የጭነት አገልግሎት 6. የወረዳ አስተዳደሩ የውስጥ ካፌ አገልግሎት 7. ኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ እቃዎች ጥገና 8. የተለያዩ የህትመት ስራዎች 9. የጉልበት/ጫኝና አውራጅ ስራዎች የመሳሰሉትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. የታደሰ ንግድ እና ምዝገባ ፈቃድ ያለው
2. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
4. በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን ማስረጃ ያለው ለሚመለከው ዘርፍ
5. በዘርፉ ከዚህ በፊት በነበረው አፈጻጸም የድጋፍ ደብዳቤ ያለው
6. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /VAT/ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ፋ/ጽ/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላል።
8. የጨረታ ማስከበሪያ ብር አላቂ እቃ ሎት 1/ 29,000 (ሀያ ዘጠኝ ሺህ ብር) ጽዳት ሎት 2/ 20,000 ( ሀያ ሺህ ብር) ኤሌክትሮኒክስ ሎት 3/ 29,000 (ሀያ ዘጠኝ ሺህ ብር) የደንብ ልብስ ሎት 4/ 36,000 (ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር) ቋሚ እቃዎች ሎት 5/ 15,000 ( አስራ አምስት ሺህ ብር) የቋሚ እቃ ጥገና ሎት 6/ 17,500 ( አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሎት 7/ 17,500 (አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) ትራንስፖርት ሎት 8/ 47,000 ( አርባ ሰባት ሺህ ብር) ህትመት ሎት 9/ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ካፌ መስተንግዶ ሎት 10. 85,000 (ሰማንያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ cpo ማስያዝ የሚችል።
9. የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት ተጠቅሶ በግልጽ መጻፍ ይኖርበታል።
10. የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽገው ኦርጅናሉን ኦርጅናል ኮፒውን ኮፒ በማለት ሁለቱንም በA4 ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የትኛውም ቦታ ላይ ማህተም እና ስም ሲጽፉ የድርጅቱን ስም ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል።
12. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉትን እቃ ትእዛዝ በደረሳቸው በ7 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት እና የማውረጃ ወጪ ወረዳ አስተዳደሩ መጋዘን ውስጥ አስገብተው ማስረከብ አለባቸው።
13. የጨረታ አሸናፊዎች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 10 ፐርሰንት በ/CpO/ በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
14. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጽፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ የመኪና እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሌሎችም እቃዎች ናሙና በቀላሉ በማይቀደድ እና ባልተጨናነቀ መያዥያ ማቅረብ ግዴታ ነው።
15. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው የሚሰሩ ነጋዴዎች የድጋፍ ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ መሆን አለበት።
16. ለናሙና በሚቀርብ ምርት ላይ የተጫራቹን አድራሻ/ ማህተም ማድረግ አይቻልም።
17. የናሙና ዝርዝር የናሙናውን ስም በአግባቡ በኮምፒውተር በስርአት መጻፍ የሚችል
18. ለመኪና ኪራይ፤ ለህትመት እና ለመስተግዶ ተጫራቾች በዘርፉ የሰሩና በሰሩበት የመልካም ስራ አፈጻጸም ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
19. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ በዚሁ ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የጨረታ ሳጥን ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ።
20. ሌሎች በዚህ ያልተጠቀሱ ህጎች በግዥ አዋጅ እና መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ይሆናሉ።
21. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፡- የተባበሩት አደባባይ /AICC/ አዲስ ኮንቬሽን ሴንተር ጀርባ
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 011 667 8556
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 13 አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ በዚሁ ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-01 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ በሚቀጥለው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 13 አስተዳደር
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T08:28:20.000Z
- Source: 2merkato