Packaging and Labelling

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ አገልግሎቶች ግዥ፣ የተለያዩ እቃዎች ግዥ እና ያገለገሉ እቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የዘር አሰባሰብና የቀጥታ ዘር ግብይት ዘር ለማሰራጨት የተለያዩ ምርጥ ዘሮችን ከተለያዩ ወረዳዎች ወደ ዘር ማበጠሪያና ማከማቻ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ፣ የሰብል ጥበቃ ቁሳቁስና የተለያዩ ኬሚካሎች ግዥ፣ የዘር ማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ ግዥ፣ የላብራቶሪ ማቴሪያል ግዥ፣ የዘር ማሰባሰቢያ ጆንያ፣ የዘር ማሸጊያ ከረጢት ለማሳተም እና ለዘር ማሰባሰብ የሚዉሉ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እና የፈርኒቸር እቃዎች ለማስጠገን እና የተለያዩ ለዘር የማይሆኑ ሰብሎች የተለያዩ ብጣሪዎች፣ ያገለገሉ ጆንያዎችን እና ያገለገሉ እቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

1. የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር/ቢሮ/ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የመኪና ባለቤትነት ማረጋገጫ እና የመጫን ችሎታ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የማበጠሪያ ማሽን መለዋወጫ ለማቅረብ ፈቃድ የተሰጠዉና ከ2 ወር ባልበለጠ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የደረቅ ጭነት ማመላለሻ መኪኖች ያሉዋቸው የመኪኖችን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ከዋናው ጋር የተረጋገጠ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ሲጠየቅ ዋናውን ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት  ባሕር ዳር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡

9. የተለያዩ ንፁህ ሰብሎች የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡

10. ግዥዉን ባሕር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዘን መድሐኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ዝርዝሮችን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ በአለ በጅምላ ግቢ ዉስጥ በሚገኘዉ በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ 10ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡

12. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን እስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

13. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582266002 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583208415 ወይም 0918016935 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-10 17:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Seed Enterprise
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Be'kur (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T09:17:40.000Z
← Back to all tenders