Music and Entertainment

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ለ2019 በጀት ዓመት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ መልክ ለተዋቀረዉ የማርሽ ባንድ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የማርሽ ባንድ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የተለያዩ አይነት የማርሽ ባንድ  ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ  የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር (አንድ) 01/2019

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ለ2019 በጀት ዓመት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ መልክ ለተዋቀረዉ የማርሽ ባንድ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የማርሽ ባንድ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች -

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምሥክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፍኬት ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የትብብር ደ/ቤ ማቅረብ የሚችል

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond/ ለሚያቀርቡት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 2%  /CPO/ ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው የተሞላዉ ዋጋ ከዘጠና ቀናት(90) በታች መሆን የለበትም።

4. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

5. የቴክኒካል ስፔስፍኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ፋይ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

7.ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ ጨረታዉም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽነ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

9. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ዉል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

10. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ዉል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ባለዉ ጊዜ ዉስጥ 25% የመጨመር መብት አለዉ።

11. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ሞባይል ቁጥር 09 10 06 29 54 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
ሆሳዕና


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 06፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-29 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 08፡00 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Police Commission of the Government of Central Ethiopia
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 50 (ሃምሳ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:03:18.000Z
← Back to all tenders