Stationery

ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ. በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለህትመት አገልግሎት የሚውል አርት ወረቀት ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፣ ሜልባ/ብ/ግ/ጫ/001/2019

ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አ.ማ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለህትመት አገልግሎት የሚውል አርት ወረቀት ለመግዛት ይፈልጋል

ተ.ቁ

የእቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስያዣ መጠን

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አርት ወረቀት250 ግራም 61*86

ሪም

20,000

የአጠቃላይ ኮንትራት ዋጋ 1% ግን ከ500,000.00 ብር ያልበለጠ

26/12/2018 ከቀኑ 8፡00

26/12/2018 ከቀኑ 8፡10

 

በዚህ መሰረት፡

1. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች አግባብነት ያለው የ2018 የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፤ በጨረታው መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ከሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ምዝገባ (suppliers list) ላይ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋና ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ መ/ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ9ዐ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።

4. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናውንና ቅጅ በተለያየ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም በአንድ ላይ በሚይዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት 2ኛ ህንጻ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

6. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ሜልባ ፕሪንቲንግ ፐብሊሺንግና ፓኬጂንግ አማ

ቦሌ ሚካኤል ኢጃ ዴቬሎፐር ህንጻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ አጠገብ

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ. 251 011 855 0083 / +251 91 196 8780

ፊንፊኔ ኢትዮጵያ

ሜልባ ፕሪንቲንግ፣ፐብሊሲንግና ፓኬጂንግ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-01 14:10
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Melba Printing, Publishing & Packaging S.C.
  • Buyer address: ቦሌ ክ/ከተማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ግቢ አጠገብ
  • Bid bond: የአጠቃላይ ኮንትራት ዋጋ 1% ግን ከ500,000.00 ብር ያልበለጠ
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:20:25.000Z
← Back to all tenders