Materials

በየካ ክ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በልዩ ልዩ ሎት የወጡ እቃዎችን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በልዩ ልዩ ሎት የወጡ እቃዎችን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ የሚከተሉትን ከ1-10 ያሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ሟሟላት ይኖርባችኋል፡፡

1. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባና የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቫት ተመዝጋቢና ካሽ ሪጅስተር ያለው፤ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ/በመክፈል ከት/ቤቱ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ለጨረታ ማስረከቢያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO/ ከሎት አንድ እስከ ሎት ሶስት ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000.00(ሀያ ሺህ)፤ ከሎት አራት እስከ ሎት ሰባት ለእያንዳንዳቸው ብር 12,500 (አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ)፣ ለሎት ስምንት እና ዘጠኝ ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000 (አስር ሺህ)፣ ለሎት አስር፣ አስራ አንድ እና አስራ ሁለት ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000 (አስር ሺህ) ለሎት አስራ ሶስት፤ አስራ አራት እና አስራ አምስት ለእያንዳንዳቸው ብር 5,000 ከጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡

4. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በታሸገ ፖስታ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናልና ኮፒ እሽግ ለይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፤

5. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡

6. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በማግስቱ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ ፣ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው ይከፈታል፡፡

7. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ሎት ከንግድ ፈቃዳቸው ጋር ተዛማጅ ወይም በዛ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡

9. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ሰነድ ላይ ̇ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንጂ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡

10. ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ባሉት ሥራ ቀናት ውሰጥ ለሚወዳደሩበት ዕቃ በየአይነቱ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡

11. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጃችሁ የንግድ ዘርፍአችሁን የሚገልጽ ደብዳቤ አጽፋችሁ ማምጣት ይኖርባችኋል።

12. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ የእቃው ዋጋ ከቫት በፊት ቫት፣ጠቅላላ ዋጋ ተብሎ በተገለጸው ቦታ በትክክል መሙላት አለባቸው፡፡

13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻችን፦ ኮተቤ ደጃዝማች ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስተጀርባ በኩል 300 ሜትር ገባ ብሎ ሲሆን ለበለጠ መረጃ ደጃ ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ

ስልክ ቁጥር 011 645 6199

በየካ ክ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በማግስቱ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በማግስቱ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dejazmach Wondyerad General Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:35:06.000Z
← Back to all tenders