House and Building Foreclosure
የቦታው ስፋት 815ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለሙበት ሲ/ር ሙኒራ በክሪ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሚስስ ቬሬና በክሪ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 323907 በ04/03/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/143405 በ03/7/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 07 በሀቢታት ኒው ፍላወር ሪል እስቴት የሆነ በዶ/ር በክሪ አብዱላሂ ቱኔ ስም በይዞታ መለያ ቁጥር AA000070704889 የተመዘገበ መኖሪያ ቤት የቦታ ስፋት 815ካ/ሜ የቤቱ ስፋት 421.88 ካ/ሜ 143.17 ካ/ሜ መንገድ ጥናት ይነካዋል ከሁለቱም መንገድ አቅጣጫ በኩል 2 ሜትር ሴት ባክ መጠበቅ ስለሚኖርበት የቦታው ስፋት 667.83 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 22,647,755 (ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ አምስት) ብር ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉነ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4 አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-09-21 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
- Posted at: 2026-08-14T08:36:09.000Z