Cleaning and Janitorial Equipment and Service

ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ የስፖርት መምህራን ትጥቅ፣ የመረብ ኳስ፣ የእግር ኳስ፣ የመምህራን ጋወን፣ የጥበቃ እና የፅዳት የደንብ ልብስ፣ የላብራቶሪ ወንበርና ጠርጴዛ፣ ኮንፒውተር መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ/ም

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣የስፖርትመምህራን ትጥቅ፣ የመርብ ኳስ፣ የእግር ኳስ፣ የመምህራን ጋወን የጥበቃ እና የፅዳት የደንብ ልብስ የላብራቶሪ ወንበርና ጠርጴዛ፣ኮንፒተር መግዛት ይፈልጋል።

1/የደንብ ልበስ ሎት 1 ለጨረታ የሚያሲዙት የብር መጠን 15,180

2/ አላቂ የፅዳት እቃ ሎት 2 ለጨረታ የሚያሲዙት የብር መጠን 10,400

3/ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 3 ለጨረታ የሚያሲዙት የብር መጠን 6000

4/ አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 4 ለጨረታ የሚያሲዙት የብር መጠን 4950

5/ አላቂ የትምህርት እቃ ሎት 5 ለጨረታ የሚያሲዙት የብር መጠን 10275

6/ ፕላንት ማሽነሪ መግዣ ሎት6 ለጨረታ የሚያሲዙት የብር መጠን 7500

7/ ለህንፃና ቁሳቁስ መግዣ ሎት7 ለጨረታ የሚያሲዙት የብር መጠን 5500

የተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴትታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በCPO ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ለእያንዳንዱ በተቀመጠው የብር መጠን መሰረት ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀበት በ5 ቀን ውስጥ ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፣

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ከት/ቤቱ ሂሣብ ክፍል የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሰረት በ7 ቀን ውስጥ እቃዎቹን ለት/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ክፍል ሀላፊ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ሠነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎችን ተቋሙ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ አድርገው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እስከ ሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሁሉም ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያተካተተ መሆን አለበት።

ጨረታው የሚታሸገው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን በዛኑ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል ። ት/ቤቱ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው።

አድራሻ፡- ኮተቤ ኪዳነምህርት መውጫ 300 ሜትር ገባ ብሎ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 673 4127

ራዕይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Raey Primary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
  • Posted at: 2026-08-14T08:38:01.000Z
← Back to all tenders