House and Building Sale
በድጋሚ የወጣ የቦታው ስፋት 269.5 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ሸዋዬ ሰኚ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ኢደኤ ሰኚ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/113312 በ26/7/2016 ዓ.ም እናመ/ቁ/115507 በ23/11/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቤ.ቁ አዲስ የካርታ ቁጥር 010150/B የሆነ ቤት G+3 መኖሪያ ቤት ፍርድ ያረፈበት ቤት ይዞታ መለያ ቁጥር AA000070807445 የተመዘገበ የቦታው ስፋት 269.5 ካ/ሜ ቤት ከጠቅላላው ይዞታ ላይ 22 ካ/ሜ መንገድ ጥናት የሚቆርጠው ቤቱ/ይዞታው/የ4/አራት/ ዓመት የቦታና የቤት ግብር ዕዳ ያለበት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 16,005,944.50 (አስራ ስድስት ሚሊዬን አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ብር ከ50 ሳንቲም) ሆኖ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ በእለቱ ተጫራች አልቀረበም፡፡ ይህንኑ ለፍ/ቤቱ ሪፖርት ተደርጎ ፍ/ቤቱ በ21/5/2018 ዓም በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ትዕዛዝ የሰጠ በመሆኑ በሁለተኛ ጨረታ የሚያዘው እኛ ብር 4,001,486.125 (አራት ሚሊዮን አንድ ሽህ አራት መቶ ሰማኒያ ስድስት ብር 12/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-21 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 14, 2026)
- Posted at: 2026-08-14T08:41:24.000Z