Equipment and Accessories
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (NCO) ለዋና ጽሕፈት ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እድሳት፣ የቅብ (Painting)፣ የኤሌክትሪክ፣ የሳኒተሪ (Sanitary) መስመሮች ጥገና እና የተለያዩ የዲዛይን/ማስጌጫ አክሰሰሪዎች አቅርቦትና ገጠማ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
Bid Notice (የጨረታ ማስታወቂያ)
የጨረታ ቁጥር፡ NCO/0298/26
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (Natanim Charitable Organization)
- የቢሮ እድሳት፣ የቅብ፣ የኤሌክትሪክ፣ የሳኒተሪ እና ተያያዥ ሥራዎች ግዢ ጨረታ
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (NCO) ለዋና ጽሕፈት ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እድሳት፣ የቅብ (Painting)፣ የኤሌክትሪክ፣ የሳኒተሪ (Sanitary) መስመሮች ጥገና እና የተለያዩ የዲዛይን/ማስጌጫ አክሰሰሪዎች አቅርቦትና ገጠማ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1.1 ስለ ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት (Natanim Charitable Organization - NCO)
ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት (NCO) በሚያዚያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. (License No. 6792) የተመዘገበ ኢትዮጵያዊ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ በአእምሮ ጤና፣ በማህበራዊ ድጋፍ (Psychosocial Support) እና አካል ጉዳተኞችን በማካተት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል።
I. የሚፈለጉ ዋና ዋና የሥራ ዝርዝሮች (Scope of Work Summary)
- የቅብ ሥራዎች (Painting Works): የእጅ መያዣ (Handrail) የሁለት እጅ አንቲረስት እና ፕላስቲክ ኢመልሽን ቅብ፣ እና የውስጥ ግድግዳዎች የሶስት እጅ ፕላስቲክ ኢመልሽን ቅብ ሥራ።
- የሳኒተሪ መስመር ጥገና (Sanitary Line Maintenance): በሽንት ቤትና በኩሽና ውስጥ ያሉ የሳኒተሪ መስመሮችን መጠገን እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን አሟልቶ መግጠም።
- የኤሌክትሪክ ጥገና እና ገጠማ (Electrical Maintenance & Installation): በኮሪደር፣ በመግቢያ እና በሪሴፕሽን አካባቢ የመብራት እና ስፖት ላይቶች ገጠማ።
- አክሰሰሪዎች እና የምልክት ሰሌዳዎች (Accessories & Signage): የፎም ቦርድ አርማ (Foam Board Signage)፣ የግድግዳ ላይ የአበባ ማቀፊያዎች (Fiber board hangs with green pots) እና የምስክር ወረቀት ፍሬሞች ገጠማ።
- የአየር ማወጫ/መምጫ (Ventilation/Exhaust Fans): ለሽንት ቤት እና ለኩሽና የኤግዞስት (Exhaust/Suction) ሲስተሞች ገጠማ።
II. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ: በዘርፉ (በኮንስትራክሽን፣ ሕንፃ እድሳት ወይም አጠቃላይ ጥገና) የተሰማሩበት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ግብር ከፋይነት: የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የሥራ ልምድ: ተመሳሳይ የቢሮ እድሳት እና የጥገና ሥራዎችን በጥራት የመስራት ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው።
- የዋጋ ተመን (BOQ): የቀረበውን የቢል ኦፍ ኳንቲቲ (BOQ) መሠረት በማድረግ ዋጋቸውን በኢትዮጵያ ብር (ETB) በVAT ያካተተ ወይም ያልያዘ መሆኑን በግልጽ መጥቀስ አለባቸው።
III. የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ የጊዜ ሰሌዳ
- የጨረታው ማስታወቂያ የሚወጣበት ቀን: አርብ፣ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም / August 14, 2026
- የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ሰኞ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. / Monday, August 24, 2026 ከቀኑ 11:00 ሰዓት በፊት።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን፡ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. / Tuesday, August 25, 2026 ከቀኑ 5:30 ሰዓት ላይ።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል) በሁለት የተለያዩ ኤንቨሎፖች አሽገው፣ በአጠቃላይ በሶስተኛ ፖስታ ውስጥ በማሸግ በናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላሉ። ማሳሰቢያ: ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ እና አድራሻ
- ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (Natanim Charitable Organization)
- ስልክ፡ 0933839191 (Betelihem Kefyalew), 0993252797 (Tsedeniya Getinet), 0945462424 (Fikirte Tarekegn)
- ኢሜይል: [email protected] , [email protected] , [email protected]
- አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-08-25 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Natanim Charitable Organization (NCO)
- Buyer TIN: 0084298990
- Published on: 2merkato.com (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T06:34:36.000Z
- Buyer website: https://natanimethiopia.org/