House and Building Sale
175 ካ.ሜ G+2 የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ጋሻው መለሰ አስፋው እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አስካለ ወ/ሩፋኤል ገ/ኪዳን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 147762 በ21/07/2015 ዓ.ም እና በ13/3/2016 እና በመ/ቁ 135346 በ6/3/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ በአሁኑ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤ.ቁ አዲስ የሆነው ቤት የይዞታው ስፋት በካርታ 175 ካ.ሜ G+2 የሆነ ቤት በፍ/ባለመብትና በፍ/ ባለዕዳ ስም የተመዘገበ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 17,733,550 (አስራ ሰባት ሚሊዬን ሰባት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺ አምስት መቶ ሀምሣ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.147762 በ20/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 4,433,387.50 ( አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ሰባት ከ50/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግአለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-25 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T08:02:58.000Z