Stationery

በልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ የጥገና እቃዎች፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃ፣ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የሕትመት ሥራዎች እና ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ የጥገና እቃዎች አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት ዕቃ፤ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የሕትመት ሥራዎች እና ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚህም መሰረት፡-

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።

2. በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል

3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በጤና ጣቢያው እረዳት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 40 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 2 የጥገና ዕቃ 15,000 ሎት 3 የጽሕፈት ዕቃ 23,000, ሎት 4 ህትመት ሥራ 22,500 ሎት 5 ደንብ ልብስ 20,000 ሎት 6 የፅዳት ዕቃ 24,000 እና ሎት 7 የቋሚ ዕቃ 42,000, እና በCPO/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡ የዕቃ አይነት (ሳምፕል) ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን እቃ ዋጋ መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የግዥውን አይነት በኤንቬሎፑ ላይ በመጥቀስና ማህተም በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ በአል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራች አባላት በተገኙበት በጤና ጣቢያው አዳራሽ ይከፈታል።

9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም

11. ጤና ጣቢያው የሚጫረተውን እቃ ብዛት እንደአስፈላጊነቱ በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች ላሸነፉት ዕቃ የአንድ ዓመት ዋስትና መስጠት አለባቸው።

12. ጤና ጣቢያው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ብስራተ ገብርኤል አደባባይ የኢ/መ/ፋ/ፊት ለፊት ልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡_ 011 834 7566 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: General Jagama Kelo Memorial Health Post
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T08:46:56.000Z
← Back to all tenders