Building Construction
በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል አዲስ የተሰራው የእናቶች እና ህጻናት ክፍል ግንባታ MCH BLOCK በጎርፍ እንደይጠቃ የመሬት ድጋፍ ግንብ RETAING WALL ማሰራት ስለፈለግን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል አዲስ የተሰራው የእናቶች እና ህጻናት ክፍል ግንባታ MCH BLOCK በጎርፍ እንደይጠቃ የመሬት ድጋፍ ግንብ RETAING WALL ማሰራት ስለፈለግን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትእና መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት/
2. የዘመኑን ግብር የከፈለ /ለች
3. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ነች
4. ጨረታው የሚከናወነው በተናጠል ነው።
5. አዲስ የተሰራው የእናቶች እና ህጻናት ክፍል ግንባታ MCH BLOCK
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሆስፒታሉ ዋና ገንዘብ ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።
6. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል።
8. የሆስፒታሉን እስፔስፊኬሽን መቀየር አይቻልም።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታውን መክፈት ይቻላል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 14 34 43 06 / 09 34 37 02 54 / 09 23 74 70 44 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
መካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-31 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Mekane Selam General Hospital
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T08:50:16.000Z