Office Machines and Accessories
በኢሉባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸሮችን፣ የደንብ ልብስና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸሮችን፣ የደንብ ልብስና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ ከዚህ ቤታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ::
2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ የሚያቀርብ (Tin No) ያለው::
3. በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
4. የሚያሸንፉበት የዕቃ ዋጋ ከብር 100,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
5. ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ 50,000 ብር በሲፒኦ ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንከ ማስያዝ የሚችል::
6. ተጫራቾቹ የመወዳደሪያ ዋጋ ሲያቀርቡ የእቃውን ሙሉ ሥም የተሠራበትን ሀገርና የጥራት ደረጃውን አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የዕቃዉን ናሙና ማቅረብ የሚችል፡፡
7. ተጫራቾቹ ጨረታዉን ካሸነፉ ዕቃዎቹን በራሱ ወጪ እስከ ኢሉባቦር ዞን በቡሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል::
8. መሥሪያ ቤቱ ለሚጠራጠራቸዉና ማጣራት ለምፈልገዉ ዕቃ ናሙና ማቅረብ የሚችል፡፡
9. ጨረታውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚሁ ቀን ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል::
10.ተጫራቾቹ የሚወዳደሩበትን በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመመልከት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ (ፖስታ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
11.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 1000 ብር ከቡሬ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 በመግዛት ዋጋውን ሞልተው ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ውሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
ማሳሰቢያ፡- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0917 791 789 / 0913 353 461 መረዳት ትችላላችሁ::
በኢሉባቦር ዞን የቡሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-09-02 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 4:00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Illubabor Zone Bure Woreda FEDB
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T09:40:57.000Z