Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ ለሚካሄደው የተለያዩ ዕቃዎችን ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር የካ/ክ/ፐ/ሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት/01/2018

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ ለሚካሄደው 1-ጽህፈት መሳሪያ እና አላቂ የቢሮ ዕቃ- 2- ጽዳት ዕቃ፤ ሎት -3 ደንብ ልብስ ፤ 4- መስተንግዶ /ቡና ሴሪሞኒ ሎት -5 የተለያዩ መጠን ያለቸው ህትመት ፡6- ሞንታርቦ ጀነረቴር ፡አዳራሽ ዲኮር እና ድንኳን ኪራይ ፡7 - ቧንባ ዕቃ 8- ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች 9- መኪና ጌጣጌጥ 10-የመኪና ክራይ 11- ፈርኒቸርና ልዩ ልዩ ቋሚ ዕቃ 12- የፈርኒቸር ጥገና 13- ኮሚፒዩተር ፎቶ ኮፒ መለዋወጫ፡ ተያያዥ የሆኑና ጥገና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ይጋብዛል።

1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ።

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ አደርጎ ማቅረብ የሚችሉ

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉያልተመዘገባቸው ከሆነ ደግሞ ከገቢዎች ድብዳቤ ማጻፍ የሚችል።

5. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ይሁን እንጅ ቁጥር 3 ላይ የተጠየቀው ላይ ድህረ ገፅ ተጠቅመን የማናይ መሆኑን እገልጻለን።

6. ተጫራቾች ናሙና እንድታቀርቡ የተጠየቁባቸዉን እቃዎች የጫረታ ሰነዶችን ሲያስገቡ የተጠየቁዉን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለበት።

7. ለተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት፡ 1 ጽህፈት መሳሪያ እና አላቂ የቢሮ ዕቃ-10,000 (አስር ሺህ ብር) ፤ሎት 2 ጽዳት ዕቃ 10,000 (አስር ሺህ) ሎት 3 -ደንብ ልብስ 10,000 (አስር ሺህ ብር)፤ ሎት 4- ፡መስተንግዶ /ቡና ሴሪሞኒ /5,000 (አምስት ሺህ ብር) ሎት -5 የተለያዩ መጠን ያላቸው ህትመት -5,000(አምስት ሺህ ብር)፤ ሎት 6 ፡ ሞንታርቦ ጀነረቴር ፡አዳራሽ ዲኮር እና ድንኳን ኪራይ 10,000 (አስር ሺህ ብር)፤ ሎት 7-ቧንባ ዕቃ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ፤ ሎት 8፡ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 10000 (አስር ሺህ ብር)፤ ሎት 9- መኪና ጌጣጌጥ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሎት 10- የመኪና ከራይ 10,000 (አስር ሺህ ብር) 11- ፈርንቸር ልዩ ልዩ ቋሚ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሎት 12- የፈርኒቸር ጥገና 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ሎት 13- ኮሚፐዩተር ፎቶ ኮፒ መለዋወጫ፡ተያያዥ የሆኑ ና ጥገና 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በየካ/ ክፍለ ከተማ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወ.ዘ.ተ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋለ፡፡ እያንዳንዱ ሎት ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ/በመግዛት ይቻላል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራ ፐ/የሰ/ሀ/ል ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ በስተቀኝ መሃል መንግስት ግዥ ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከ1-4 የተዘረዘረዉን ኮፒውን ተቋሙ የሸጠዉ ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናልና ቴክኒካል ኮፒ በተጨማር ፋይናሽያል ኦርጅናልና ኮፒ ጋር በተለያየ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች ተቋሙ በሸጠዉ ሰነድ መመለስ አለባቸዉ ከዛያ ዉጪ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

9. ተጫራቾች የሚያቀረቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።

10. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ 10% የዉል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

11. የጨረታ ሳጥን በ11ኛውቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

12. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ተጫራቾች ለምታቀርቧቸዉ ናሙናዎች የምታመጡባቸው እቃዎች ጠንካራ አና በቀላሉ ሊቀደዱ የማይችሉ /ማዳበሪያ ከረጢት / መሆን አለባቸው በፌስታል የሚመጡ ናሙናዎችን አንቀበልም።

አድራሻ፡- መገናኛ ውበት ህንፃ /ማራቶን ህንፃ/ፊት ለፊት የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 7ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር- 0968 775 266 / 0939 998 138

አዲስ አበባ

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Public Service and Human Resource Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T09:49:56.000Z
← Back to all tenders