Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በሸገር ሲቲ ገላን ክፍለ ከተማ የአንዶዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚወሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችና፣ የምልሻ ሙሉ የደንብ ልብስ ማለትም ጫማ፣ ካልሲ፣ ቀበቶ እና የውስጥ ቲሸርት ግዢ ከአገር ውስጥ ተጫ

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፤ 01/2019

በሸገር ሲቲ ገላን ክፍለ ከተማ የአንዶዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚወሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ ፣የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችና ፣የምልሻ ሙሉ የደንብ ልብስ መለትም ጫማ፣ ካልሲ፣ ቀበቶ ፣ የውስጥ ቲሸርት ግዢ ከአገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ፤ በጨረታው መሰረት ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አማልተው መገኘት ይኖርባቸዋል።

1. በንግዱ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

2. የመንግሥት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

3. በመንግሥት ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ የደንብ 10,000.00 ብር (አስር ሺ ብር) ለሎት ሁለት የጽሕፈት መሣሪያዎች 10,000.00 ብር (አስር ሺ ብር) ለሎት ሶስት የፅዳት ዕቃዎች 3,000.00 ብር (ሦስት ሺ ብር) ለሎት አራት የመኪና ጎማዎች 7,000.00 ብር (ሰባት ሺ ብር) ለሎት አምስት ፈርኒቸሮች ና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 10,000.00 ብር (አስር ሺ ብር) ለሎት ስድስት የትምህርትና ሙያ ሥልጠና መሣሪያዎች 3,000.00ብር (ሦስት ሺ ብር) ሕጋዊ ከሆነ ባንክ የተረጋገጠ CPO ከሚያቀርባቸው ሰነዶች ጋር መያያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር በየእቃው ምድብ ዓይነት (ሎት) ለደንብ ልብሶች፣ ለጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ለፈርንቸሮች፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለእያንዳንዳቸው ሎት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ አምሳ ብር) እና ለሌሎች ሎት 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአንዶዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የሚያቀረቡትን ዋጋ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን እስፔስፍኬሽን (specification) ሳይቀየር ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡ 30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ዕለት 5፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ወይም ሁለቱም ካልተገኙ ታዛቢዎች በሚገኙበት ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቁጥር 5 በተገለጸው ቦታ ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች ናሙና ለማቅረብ ከሚያስቸግሩ እቃዎች ውጭ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፊው በአሸነፈባቸው ዕቃዎች ላይ 10 (አስር) በመቶ ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በሕጋዊ ባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ መሸነፉ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ ቀናት ውስጥ አንዶዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመገኘት ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተራ ቁጥር 8 ላይ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ውል የማይፈጽም አሸናፊ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ የሚደረግ ሆኖ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።

11. አሸናፊው ውል ፈርሞ በውል ስምምነት መሰረት ከላይ በተገለጸው አድራሻ በራሱ ትራንስፖርት እቃዎቹን አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል።

12. በጨረታ ውል መሰረት እቃዎቹን በሙሉ ካሰረከበ ክፍያው ወዲያው ይፈጸማል።

13. መሥሪያ ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ወይም ከውስጡ በመተው ማዘዝ ይችላል።

14. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ የስልክና ሞባይል ቁጥር በትከክል ጽፈው ማህተም በማድረግ መፈረም አለባቸው።

15. መ/ቤቱ የተሻላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 09-10-96-06-86 / 09-12-68-54-18

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክፍለ ከተማ የአንዶዴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-01 11:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: South West Gelan Sub City Andode Finance Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T09:56:49.000Z
← Back to all tenders