House and Building Sale

ስፋቱ 100.8 ካ.ሜ. የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ አለምይብራ ያለው እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ሰመረ ያለው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 191513 በ05/02/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/204228 በ26/03/2017ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/216023 በሚያዚያ 26 ቀን 2018 በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዲስ 100ካ/ሜ ላይ ያረፈ ሰነድ አልባ ቤት እና ይዞታ ይዞታው ሰነድ አልባ ነው ቦታው ስፋት 100.8 ካ/ሜ ቤቱን የሚያዋስኑትበስተፊትለፊት መንገድ በስተቀኝ አላ ምስጋናው ያለው በስተግራ ጌታነህ ስንሻው በስተጀርባ አበራ በቀለ የሚያዋስኑት ሆኖ ቦታው የመንገድ ጥናት የሌለው ሆኖ ቦታው ለTVET /ለቴክኒክና ሙያ /የቦታ አተም ውስጥ የሚገኝ ቦታው መንገድ ጥናት የሌለው እንዲሁም በ1988 በጂ አይ ኤስ 1997፤ በ2003 አየር መስመር ላይ ጭምር የማይታይ መሆኑን እና ለ3ኛ ወገን ስም ለማዞር በመመሪያ መሰረት የማይቻል ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር  4 ,146,876.8 ( አራት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ስድስት ከ80/100) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛውን አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-22
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-22 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T09:58:35.000Z
← Back to all tenders