Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የወንጪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2019

መሥሪያቤታችን በወረዳችን ለሚገኙ መስሪያቤቶች የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎችን፡ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፡ ቋሚ ዕቃዎች ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ፡ የደንብ ልብስ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች –

1. የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና የVAT ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ለጨረታው ማስከበረያ ዋስትና (Bid bond) ብር 30,000.00 (ሳላሳ ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ካሽ(cash) ከሚያቀርቧቸው ሰናዶቻቸው ጋር ማስያዝ አለባቸው።

3. በወጣው ጨረታ ሰነድ ላይ መ/ቤቱ ማስተካከያ መጠየቅ የሚችል መሆኑን፡

4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00(አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን ወንጪ ወረዳ ገቢዎች ባለ ሥልጣን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

5.ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ሰነድ ዋጋ ኦሪጅናልና ኮፒውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ በወንጪ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው ሣጥን እስከ 26/12/2018 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በ 26/12/2018 ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ለይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወንጪ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ይከፈታል።

7. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀ በኋላ የግዢ አፈጻጸም ውል ይዋዋላል ።የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በቅድሚያ ያስይዛል::

8. ተጫራቹ ጨረታውን ያሸነፈበትን ዕቃዎች ወንጪ ወረዳ ጭቱ ከተማ ከወሊሶ 9ኪ.ሜ ላይ በሚገኘው የገንዘብ ጽ/ቤት በራሱ ትራንሰፖርት አድርሶ ያስረክባል።

9. በጨረታው ውል መሠረት አሸናፈው ዕቃዎቹን በሙሉ ሲያስረክብ ክፍያው ወዲያው ይፈጸማል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.ተጫራቾች ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ዓይነት እና ባቀረቡት ናሙና መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ስልክ ቁጥር 0113 160 099፣ 0113 161 01 ፣ 0920 138 277 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የወንጪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid opening: 2026-09-01 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: South West Shewa Zone Wonchi Woreda Finance and Economic Development Office
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T10:42:01.000Z
← Back to all tenders