Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምእራብ ሐረርጌ ዞን በቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምእራብ ሐረርጌ ዞን በቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል ኣላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት)ተመዝጋቢ የሆኑ እና ለዚሁም ማስረጃ የሚያቅርቡ መሆን አለባቸው።

4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO)ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር-በቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት መ/ቤት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

6. ጨረታው ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ 16ተኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከዚሁ ቀን 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢኖሩም ባይኖሩም በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

7. አሸናፊ ድርጅት /ተጫራቹ/ ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

8. ተጫራቾች የተፈለገውን እቃ ጥራት እና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

9. በሽያጭ ያቀረበውን እቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴው/አሸናፊ ደርጅቱ /በራሱ ወጪ እቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት።

10. የዕቃውን ማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።

11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰንድ ኦርጂናል እና ኮፒ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. ጽሕፈት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን፡- ቡረቃ ዲንቱ ገንዘብ ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0911 982 478 / 0967 857 864 / 0913 119 344

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ 16ተኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 15:00
  • Bid opening (note): ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ 16ተኛው ቀን 9፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Burka Dinto woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T10:44:45.000Z
← Back to all tenders