Stationery

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የመኪናና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች እና የቢሮ ጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 0001

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ ቤት በ2019 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት አንድ የእስቴሽነሪ እቃዎች
  • ሎት ሁለት የመኪናና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች እና
  • ሎት ሶስት የቢሮ ጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም፡-

1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ Online /በኦንላየን/ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 30000(ሰላሳ ሺ)፤ለሎት ሁለት 30000 (ሰላሳ ሺ) እና ለሎት ሶስት 20000(ሀያ ሺ) በምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሁርና አክሊል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት ግዢ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡የጨረታው ማስከበሪያው በኦርጂናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል፡፡

5. የጨረታ አሸናፊው ዕቃዎቹን እስከ ቢሮአችን የሚያጓጉዝ ወጪ በራሱ ይሸፍናል፡፡

6. ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሸጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም፡፡

7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡

8. የቫት ገንዘብ ላይ 7.5% ብቻ የሚከፈል ሲሆን ቀሪው 7.5% ለወረዳው የሚቀር ይሆናል፡፡

9. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡ 011 343 0173/ 011 343 0614 ይደውሉ
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሐዋሪያት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-25 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Gurage Zone Mihur & Aklil Woreda FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T07:31:19.000Z
← Back to all tenders