Printing and Publishing
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የተለያዩ የሲቲፒ ፕሌቶች፣ የልብስ ሳሙና፣ የእጅ/የገላ ሳሙና፣ ኦሞ፣ የመጸዳጃ ሶፍት እና ፈሳሽ ሳሙና ላርጎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የሀገር ውስጥ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ኃ.የተ.የግ.ማህበር የተለያዩ የሲቲፒ ፕሌቶች፣ የልብስ ሳሙና፣ የእጅ/የገላ ሳሙና፣ ኦሞ፣ የመጸዳጃ ሶፍት እና ፈሳሽ ሳሙና ላርጎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመከፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንከ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ የባንክ ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ዶክመንቶቻቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አዘጋጅቶ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በድርጅቱ የግዥ ከፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
5. ተጫራቾች ለሚሳተፉበት እቃ ለጥራት ሙከራ የሚሆን ናሙና አስቀድሞ ወይም ጨረታው በሚከፈትበት እለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ጨረታው በ15ኛ የስራ ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አድራሻ ይከፈታል።
7 ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ኃ.የተ.የግ.ማህበር
ስልክ ቁጥር 011 151 5 5005/ 011 551 8872
ፋክስ....011 551 8696
ፖሳቁጥር.........2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ የስራ ቀን 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-31 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ የስራ ቀን 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Printing P.L.C.
- Buyer address: ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T07:53:32.000Z