Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የስፖርት ማሽን ጥገና ዕቃዎች፣ ሳውንድ ሲስተም ሚክሰር እና ቅርጫት ኳስ ሪንግ ጥገና ዕቃዎችን እና የምግብ ግብዓቶች አቅርቦት ለአንድ ዓመት መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር (01/2018) ዓ.ም

የተጫራቾች መመሪያ፦

የአራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የስፖርት ማሽን ጥገና ዕቃዎች ፣ ሳውንድ ሲስተም ሚክሰር እና ቅርጫት ኳስ ሪንግ ጥገና ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል። እና የምግብ ግብዓቶች አቅርቦት ለአንድ ዓመት መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን መሟላት አለባቸው።

1. ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ፣ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች በሙሉ ሆነ በከፊል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዕቃ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፤  ለሚመለከተው አካልም በደብዳቤ ይገልፃል።

3. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ፣ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።

4. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፣ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መገለጽ አለበት።

5. ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ከአራት ኪሎ ስፖ ትም/ስል ማዕከል የፋይና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል።

6. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስር የሥራ ቀናት ማግኘት የምትችሉ ሲሆን፤ ጨረታ ሳጥኑ ቀን በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡00 ይከፈታል፤ በማግስቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይናንስና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ሰነዱን ማስገባት ይኖርባችኋል።

8.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ ለማስገባት ሲመጡ የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው በግልጽ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም መረጃ ዶክመንት አንቀበልም።

10. ለአሸናፊዎቹ ክፍያ የሚፈጸመው የተጠየቀውን ዕቃ በተጠየቀውና ባሸነፋው ናሙና መሰረት ሙሉ በሙሉ ገቢ ከተደረገ በኋላ መሆኑን እናሳውቃለን።

11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃዎችን ዋጋ በማስፈር የማቅረብ እና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ ይጠበቅበታል ።

13. አሸናፊው ድርጅት ከመሥሪያ ቤቱ ጋር ላሸነፉት የዕቃ ለማቅረብ የውል ስምምነት ይፈርማል።

14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

15. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሲፒኦ/ CPO/ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ማስያዥ ይኖርባቸዋል።

16. ተጫራቾች ከአሸናፉ በኋላ የውል ዋስትና 10% ሲፒኦ (CPO) ከባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ የሚችል።

አድራሻ ፡- አራት ኪሎ ስፖርት፤ ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 7 ከሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ስልክ 01 11 261365/ 01 11 23 35 33 to

የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arat Kilo Sport Eduction and Training Center
  • Buyer address: አራት ኪሎ ስፖርት፣ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 8 ከስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አጠገብ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጅንሲ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T07:55:55.000Z
← Back to all tenders