Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የሰበታ አዋስ ወረዳ ፍ/ቤት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት አቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰበታ አዋስ ወረዳ ፍ/ቤት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት አቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ከ100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /Vat/ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መክፈል ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈለጉት ለምን ለምን ዓይነት እቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።
6. ፍ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/ በታች መቅረብ አይችልም።
7. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም።
8. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን እቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው 25% ብር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
9. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ይሆናል፤ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በነገታው በ4፡ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
10. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን በቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% የጨረታ ማከበሪያ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።
11, ፍርድ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ -ሰበታ ከተማ ጨፌ ወረዳ / 07 ቀበሌ ከሰበታ ትልቁ መስጊድ ወረድ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 011-3_338-41-09/011-338-0003/0928-99-95-70
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-03 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በነገታው በ3፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sebeta Awas Woreda Court
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T07:59:26.000Z