House, Building and Warehouse

በሸገር ከተማ አስተዳደር የቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የቡራዩ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቄራ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የቄራ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018

በሸገር ከተማ አስተዳደር የቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የቡራዩ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቄራ ለማከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በስንቄ ባንከ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1065422441218 የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ከቡራዩ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በማስቆረጥ ከቡራዩ ከተማ ገንዘብ ጽ/ ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በሚያቀርቡት በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን፣ እንዲሁም በፌዴራል ገ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ዝቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና  አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና በዘርፉ ከክልሉ የእንስሳት ጤና ኤጀንሲ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአገልግሎት ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ከጨረታው ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3. በስሙ የተመዘገበ ከ7 ቫን የሥጋ መኪናዎች ሊብሬ በተወዳዳሪው ስም ያለው ማቅረብ የሚችልና ወይም ከዚያ በላይ ያለው እና በሥጋ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታው ሰነድ በግልጽ ቴክኒክ እና ፋይናሽያል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በፖስታው ላይ ተጽፎ ለየብቻው ታሽጎ የተከራዩ ስም ተጽፎበት ማቅረብ ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የሥራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሠዓት አድራሻ በቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 107 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

6. ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 ውስጥ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

7. የጨረታው አሸናፊ ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% Performance Bonad በማስያዝ ት/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።

ማሳሰቢያ:-

  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  • አሠሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመረዝ መብቱ የተጠበቀ
  • ተጨማሪ ማብራሪያ ከተፈለገ በስልክ ቁጥር (011-260 4836) ወይም (011-260 4879) ደውለው መረዳት ይችላሉ።

በሸገር ከተማ አስተዳደር የቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የሥራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን 4:00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-09-03 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የሥራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን 4:30 ሠዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Sheger City Administration Burayu City Administration Finance Office
  • Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T08:09:29.000Z
← Back to all tenders