House, Building and Warehouse

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምርያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በኮሪደር ልማት የተሰሩ የሕዝብ መገልገያና መዝናኛ ሥፍራዎች ካፌዎችንና ሱቆቹን በጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምርያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በኮሪደር ልማት የተሰሩ የሕዝብ መገልገያና መዝናኛ ሥፍራዎች ካፌዎችንና ሱቆቹን በጨረታ ለማከራየት በድጋሚ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማከራየት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ማህበራት መካከል አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት-

  1. በዘርፉና ተመሳሳይ የሥራ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው.
  2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
  4. በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት።
  5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
  8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  10. አንድ ተጫራች በስሙ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም።
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡-046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ልማት መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-28 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:24:14.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders