House, Building and Warehouse

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሥር የሚገኙ የንግድ/ድርጅት ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የ17ኛ ዙር የንግድ/ ድርጅት ቤቶች ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ ኮ/ብ.ግ./አገ/18/02/2019

1.የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር የሚገኙ የንግድ/ ድርጅት ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ. ግ ጨ/አገ/18/02/2019 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የንግድ /ድርጅት ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ የኪራይ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው።

4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል። የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚከናወን ይሆናል።

6. ተጫራቾች የንግድ ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።

7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0910-48-59-48 ወይም 0922-98-76-33 ወይም 0922-49-18-85 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ PO. Box 299

ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-20
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-11-20 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Housing Corporation
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
  • Posted at: 2026-11-06T08:44:31.000Z
  • Buyer website: https://www.fhc.gov.et
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders