House, Building and Warehouse
የኢትዮጵያ ፐብሊከ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በባለቤትነት የሚያስተዳድረውን ካፍቴሪያ እና የወንዶች ጸጉር ቤት ኪራይ አገልግሎት ሺያጭ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፐብሊከ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በባለቤትነት የሚያስተዳድረውን ካፍቴሪያ እና የወንዶች ጸጉር ቤት ኪራይ አገልግሎት ሺያጭ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
1. የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ
የካፍቴሪያ ኪራይ፡
ጠቅላላ ካሬ ስፋት፡ 291 ካሬ ሜትር
የአገልግሎት አይነት፡ ለንግድ
የወንዶች ጸጉር ቤት ኪራይ፡
ጠቅላላ ካሬ ስፋት፡ 32 ካሬ ሜትር
የአገልግሎት አይነት፡ ለንግድ
2. ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች
ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ቲን፣ቫት፣የንግድ ምዝገባ እና የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታ ሰነድ አወሳሰድና አቀራረብ
ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 202 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርበታል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. አጠቃላይ መመሪያዎች
ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-646-33–15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች የሚከራዩትን የካፍቴሪያ እና የወንድ ጸጉር ቤት ኪራይ አገልግሎት አስቀድመው መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣ የቀረበው የኪራይ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ሲ.ኤም.ሲ መንገድ(ሰአሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ)
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
Tender details
- Deadline: 2026-11-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-16 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Public Service University
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T09:28:31.000Z
- Source: Qelal Tenders