House, Building and Warehouse
ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ለንግድ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች በግልፅ ጨረታ አጫርቶ ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የፈለጉትን በአንድ ቦታ የሚያገኙበት ከሁሉም አቅጣጫ ምቹ ቦታ የሚገኝ ለንግድ ተመራጭ የሆነ ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባ ስቴድየም አከባቢ የሚገኝ 2B+G+M+11+ቴራስ ህንፃ (ይሓ ሲቲ ሴንተር) ለንግድ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች በማከራየት ላለፉት 13 ዓመታት የህንፃ ክራይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በህንፃው 3ኛ ወለል 303.85 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ክፍል እና የውጭ ቴራስ ዙርያመለሽ ወደ ዋናው መንገድ ከሜክስኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኝ ጥሩ እይታ ያለው በመሆኑ ለካፌ እና ሬስቶራንት ተመራጭ ያደርገዋል።
የበረንዳው ሼድ (148.68) ካሬ ስፋት እና የውስጥ ይዞታ (Interior Design) ራሱ ሰርቶ በጨረታ መነሻ ዋጋ በካሬ ብር 1,100.00 (አንድ ሺ አንድ መቶ ብር ከ00/100) በግልፅ ጨረታ አጫርቶ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አዲስ አበባ ስቴድየም አከባቢ ዋና መስሪያ ቤት ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንፃ 2ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር F2/12 የሰው ሃይል አስተዳደር በአካል በመገኘት ቦታውን ማየት እና የመወዳደሪያ ዋጋ የምትሰሩት የውስጥ (Interior Design) እና ፕሮፖዛል እስከ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- አድራሻ፡- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት “ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ 2ኛ
- ፎቅ ቢሮ ቁጥር - 12
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር የቢሮ 0115580129/0115576954/
- ሞባይል - 0922079575 /0911397239
- ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-11-19 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yiha Real Estate P.L.C.
- Buyer's registered address: ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንፃ
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T08:13:08.000Z
- Source: Qelal Tenders