Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በቡኖ በደሌ ዞን የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ የሆኑና መስፈርት የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በከተማዉ ዉስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ ዉስጥ ፈርኒቸሮች፤ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የዉሀ እቃዎች፤ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች እና ባጃጅ፤ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እንዲሁም የተለያዩ
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቡኖ በደሌ ዞን የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ የሆኑና መስፈርት የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በከተማዉ ዉስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ ዉስጥ ፈርኒቸሮች፤ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የዉሀ እቃዎች፤ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች እና ባጃጅ፤ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እንዲሁም የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪ ጎማዎች መግዛት ይፈልጋል።
መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች በእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለዉና 2018 ዓ.ም ግብር ከፍሎ የ2019 ዓ.ም ንግድ ፈቃዱን ያደሰ ወይም ከገቢዎች ፅ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለዉና ማቅረብ የሚችል።
1. የቫት ( 15 % ) ተመዝጋቢ ሆኑና ማስረጃዉን ማቅረብ የሚችል።
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር መዝገብ ላይ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. በመንግስት ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ያልተከለከለ እና የተከለከለ ከሆነ የጊዜ ገደቡን የጨረሰ።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳነዱ የ ጨረታ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በስንቄ ባንክ ለበደሌ ከተማ ፋይናንስ አካዎንት ቁጥር 1071291641810 ገቢ በማድረግ ኦርጅናል ባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. በዚህ ማስታወቂያ ላይ ከተ.ቁ 1 – 4 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች መኖራቸዉን የሚያሳይ በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ በአንድ ፖሰታ ዉስጥ ታሽገዉ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ መግባት ይኖርባቸዋል።
6. የሚገዙ ዕቃዎች በጨ ረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠዉ መሰረት የሚያቀርቡበትን ዋጋ ቫትን ( 15%) ጨምሮ በጥንቃ ቄ በመሙላት በአንድ ፖሰታ ዉስጥ ታሽገዉ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ መግባት ይኖርባቸዋል።
7. አንድ ተወዳዳሪ ለአንድ ዓይነት ዉድድር ሁለት (2) ፖስታ ማስገባት ያለበት ሲሆን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ያለበትን ፖስታ የቴክኒክ በማለት እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሞላዉ የ ዋጋ መወዳደሪያ ያለበት ፖስታ ላይ የፋይናንስ (financial ) በማለት ተለይቶ መጻፍ ይኖርበታል።
8. ለማንኛዉም አይነት ጨረታ የሚሞላዉ የመወዳደሪያ ዋጋ ከነቫት መሞላት አለበት በዚሁ መሰረት ቫት (15%) ሳይጨመር የተሞላ ወይም ቫት ያስጨምራል ተብሎ የማይሞላ ዋጋ ቫት እንዳለዉ ይወሰዳል።
9. ማንኛዉም ተወዳዳሪ በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ ፊርማዉንና የድርጅቱን መህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
10. ስርዝ ድልዝ ያለዉ የቴከኒክም ሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
11. ማንኛዉም ተወዳዳሪ በጨ ረታዉ ያሸነፈባቸዉን እቃዎች በራሱ ወጪ ጭኖ እስከ በደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
12. የሠራተኞችን ደንብ ልብስ ለማቅረብ የሚወዳደር ማንኛዉም ተወዳዳሪ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የልብስ ዓይነቶች የሚያሳይ ግልጽ የሆነ ናሙና ጨረታዉ በሚከፈትበት ጊዜና ቦታ ይዘዉ መቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. በዚሁ መሰረት ሕጋዊ የሆኑና አስፈላጊዉን መስፈረት የምያሟላ ማንኛዉም ነጋዴ ይህ ማታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀን መካከል የበደሌ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመሄድ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ የበደሌ ከተማ ገንዘብ የግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት በማምጣት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ በመዉሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
14. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ15 ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ማሳሰቢያ፡- ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 047 445 2385 ላይ በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ15 ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-09-02 12:00
- Bid opening (note): ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ15 ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሠዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Bedele Town FEDB
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T11:28:52.000Z