Stationery

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የገንዘብ መምሪያ የመርሐቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የጽ/መሣሪያ እና (የመኪና እቃ በኮንትራት) በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የገንዘብ መምሪያ የመርሐቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የጽ/መሣሪያ እና (የመኪና እቃ በኮንትራት) በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1ኛ. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል::

2ኛ. የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡

3ኛ. እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በብር 400 ብር (አራት መቶ ብር ብቻ) ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት የካላንደር ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ፡፡

4ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቁርጥ ለጽ/መሣሪያ 15000 እና ለመኪና እቃው 10000 ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

5ኛ. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6ኛ, ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጐ በ3፡30 ይከፈታል፡፡

7ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8ኛ. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት መ/ቤቱ በሎትም ሆነ በነጠላ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው::

9ኛ. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-13-20-136/005 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ሕዝባዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን የገንዘብ መምሪያ የመርሐቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-31 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Merhabete Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T11:45:12.000Z
← Back to all tenders