Vehicle and Machinery Sale
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸዉንና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንኮች በተሰጠዉ ስልጣን መሠረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል።
- ተሽከርካሪዎቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ B 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፎርክሎዠርና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን ለጨረታ ባዘጋጀው ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 0711 ወይም 011 515 1153 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የተሸከርካሪዉ ዓይነትና የተሰራበት ዘመን |
የሰሌዳ ቁጥር
|
የሻንሲ ቁጥር
|
የሞተር ቁጥር
|
የተሽከርካሪዉ ሞዴል
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን
|
የምዝገባ ሰዓት
|
የጨረታ ሰዓት
|
|
1 |
አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ |
ተበዳሪው
|
የመስክ ተሽከርካሪ (ጃፓን- ቶዮታ / Toyota Landcruiser V8 VXR) (እ.ኤ.አ 2013) |
አአ-02-B78246 |
JTMHXO 5J2E4061 303
|
1UR03 99671
|
URJ200L-GNTNKV
|
12,141,740.00
|
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
|
2 |
አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ |
ወ/ሮ የአይኔብርሃን አበራ ገ/ዮሀንስ |
አዉቶሞቢል (ጃፓን-ቶዮታ /Toyota Rush-S) (እ.ኤ.አ 2021 ) |
አአ-02-C02599
|
MHKEF8 CF4NK00 8011
|
2NRG6 90752
|
F800LF-GQGFG
|
4,427,280.00
|
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም
|
8:30-9:30
|
9:30-10:00
|
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-01 16:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T12:15:17.000Z