Cleaning and Janitorial Equipment and Service

አማራ ባንክ አ.ማ. የጥበቃ ሰራተኛ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት፣ የፅዳትና የተላላኪ ሰራተኛ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመለየት ውል ስምምነት ፈፅሞ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡ አባ/ግፋማመ/ሀግጨ/025/2026

(1) አማራ ባንክ አ.ማ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ለከፈታቸው ቅርንጫፎች ከዚህ በታች የተገለፁትን አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመለየት ውል ስምምነት ፈፅሞ ማሰራት ይፈልጋል።

ሎት

የአገልግሎት ዓይነት

ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

 

I

የጥበቃ ሰራተኛ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡30 ሰዓት

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 09፡00 ሰዓት

200,000.00

 

II

የፅዳትና የተላላኪ ሰራተኛ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት

ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት

100,000.00

 

(2) ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ የአመልድ ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ፎቅ ላይ ከነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት በተጨማሪም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ) የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ / ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

(3) ተጫራቾች ከጨረታው በኃላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከላይ በተገለፀው መሠረት ከጨረታው መክፈቻ ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲፒኦ ወይም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሚሰጥ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ባንክ አ.ማ. ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

(4) ተጫራቾች የሙያ ፈቃድ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

(5) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት መሠረት ማስገባት አለባቸው። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

(6) የጨረታው ሰነድ አማራ ባንክ አ.ማ. 20ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት መግባት ይኖርበታል።

(7) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሊቲስ መምሪያ 20ኛ ፎቅ ይከፈታል።

(8) ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች አለማሟላት ከጨረታው ውጭ (ውድቅ) ያስደርጋል።

(9) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 558-2905 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

(10) ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Amhara Bank S.C.

Beyond Financing


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-01 15:30
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Amhara Bank S.C.
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Reporter (Aug 16, 2026)
  • Posted at: 2026-08-17T12:23:41.000Z
← Back to all tenders